[the_ad_group id=”107″]

ሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ “ወፍ ማስፈራሪያ እና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች” የተሰኘውን መጽሐፍ ለውይይት አቀረበ

September 21, 2015
ሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ “ወፍ ማስፈራሪያ እና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች” የተሰኘውን መጽሐፍ ለውይይት አቀረበ

ሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ በመስከረም 2008 ዓ.ም. ወርኀዊ መርሓ ግብሩ የሚካኤል ሽፈራውን “ወፍ ማስፈራሪያ እና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች” የተሰኘውን መጽሐፍ በኢትዮጵያ ሥነ መለኮት ድኅረ ምረቃ ት/ቤት መሰብሰቢያ አደራሽ  ለውይይት አቀረበ፡፡

ለውይይት መነሻ የሚሆን ጽሑፍ ያቀረበው ሠርፀ ፍሬ ስብሃት ሲሆን፣ ደራሲ ሚካኤል ይዞት የቀረበው ሥራ በኢትዮጵያ የሥነ ጽሑፍ ዘውግ ውስጥ እጁግን ያልተለመደና ተገቢውን ስያሜ እንኳን ያለገኘ እንደ ሆነ ጠቁሟል፡፡ አያይዞም፣ መጽሐፉ ዕምቅ ፍልስፍናዊ እና ሃይማኖታዊ ሐሳቦችን የያዘ ከመሆኑ ባሻገር በእንስሳት/ዕፅዋት አፍ በሚነገር የትርክት ዘዬ እውነትን የሚያስሱ ታሪኮች የታከተቱባቸው ሥራዎች መሆናቸውን አመለክቷል፡፡

የመጽሐፉ ጸሐፊ ሚካኤል ሽፈራው ከታዳሚያን ለተነሡለት ጥያቄዎች በሰጠው ምላሽ፣ ታሪኮቹ በ1987 ዓ.ም. ላይ የተጻፉ እንደነበሩና ከራሱ የግል ሕይወት ጥያቄ ተነሥቶ እንደ ጻፈው ተናግሯል፡፡ “ታሪኮቹ ተስፋን አይሰጡም፤ ጨለምተኞች ናቸው” በሚል ለተነሣለት ጥያቄ ምላሽ ሲሰጥም፣ በወቅቱ መጽሐፉን በሚጽፍበት ጊዜ የነበረበት ስሜት ይህንኑ የሚመስል እንደ ነበረ ከጠቆመ በኋላ፣ “በመፍረስ እና እንደ ገና በመሠራት ሂደት ውስጥ” ያለ ሰው ጥያቄዎችን የሚወክሉ ታሪኮች ናቸው ሲል ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ በመጪው ጥቅምት 7 ቀን፣ 2008 ዓ.ም. ለውይይት የሚያቀርበው መጽሐፍ በጸጋአብ በቀለ የተጻፈውና “የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ተሐድሶ” የተሰኘው መሆኑ ተነግሯል፡፡

በመጨረሻም፣ አያት የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) አካባቢ በሚገኘው “አያት ጨፌ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ የሕዝብ ት/ቤት” ውስጥ ለሚማሩና ቤተ ሰቦቻቸው በችግር ላሉ ተማሪዎች የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችን ለመስጠት መታሰቡንና የመጽሐፍ ክበቡ ታዳሚያን አቅማቸው የፈቀደውን ያህል እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል፡፡ በዚህም መሠረት የትምህርት መርጃ መሣሪያዎቹን በመጪው ጥቅምት 7 ቀን፣ 2008 ዓ.ም. በሚደረገው የመጽሐፍ ውይይት መርሓ ግብር ላይ ይዞ መምጣት እንደሚቻል አስተባባሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

Add comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Latest News

ስለ ቤተ መጻሕፍት አደረጃጀት ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ሥልጠና ተሰጠ

“የቤተ መጻሕፍት አደረጃጀት” የተሰኘ የግማሽ ቀን ሥልጠና ለተለያዩ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ተወካዮች ተሰጠ። በሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ አዘጋጅነት የተዘጋጀው ሥልጠና፣ ቅዳሜ ሚያዚያ 14 ቀን፥ 2015 ዓ.ም. በላቭ ኤንድ ኬር ማዕከል የተካሄደ ነበር። 

Read More »
SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.