[the_ad_group id=”107″]

ሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ የወርኀ ጥር የመጽሐፍ ግምገማ መርሓ ግብሩን አካሄደ፡፡

March 13, 2015
Logo-New-Meta-Amharic

ሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ የወርኀ ጥር የመጽሐፍ ግምገማ መርሓ ግብሩን አካሄደ፡ እሑድ ጥር 3 ቀን፣ 2007 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ድኅረ ምረቃ ት/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው ግምገማ ላይ ለውይይት የቀረበው መጽሐፍ “እኔን ማን ትሉኛላችሁ?፡- ክርስቶስ እና የማዳን ሥራው” የተሰኘውና በበልሁ ደለለኝ የተዘጋጀው መጽሐፍ ነው፡፡

በዕለቱ ሂሳዊ የግምገማ ጽሑፍ ያቀረቡት አቶ አግዛቸው ተፈራ ሲሆኑ፣ በተለይም መጽሐፉ በኦርቶዶክሳዊ ነገረ ክርስቶስ ዙሪያ የሚያጠነጥን እንደመሆኑ ገምጋሚው ትኩረታቸውን በዚያው ላይ አድርገው አቅርበዋል፡፡ ይህንንም ያደረጉት የመጽሐፉን ቅርጽ እና ይዘት በሁለት ከፍሎ በማሄስ ነበር፡፡ በዚህም፣ መጽሐፉ ጠንካራ ጎኖቹ ናቸው ያላቸውን አስቀደምው ካቀረቡ በኋላ፣ ጸሐፊው መጽሐፉን በሚያዘጋጁበት ጊዜ ያላሟሏቸው ናቸው ያሏቸውን ክፍተቶች አስከትለው አሳይተዋል፡፡

የመጽሐፉ ጸሐፊ በተገኙበት በተካሄደው በዚህ ወርኀዊ መርሓ ግብር ላይ ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣ ጸሐፊው አቶ በልሁ ደለለኝ በበኩላቸው ከገምጋሚው እና ከታዳሚያን ለተነሡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ያሉትን አቅርበዋል፡፡

ሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ በቀጣዩ ወር (የካቲት 1፣ 2007) ልዩ ዝግጅት እንደሚያሰናዳ የተገለጸ ሲሆን፣ በዕለቱ የሚኖረው ዝርዝር መርሓ ግብር በጊዜው እንደሚገለጽ ተያይዞ ተነግሯል፡፡

Latest News

SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.