[the_ad_group id=”107″]

ዘላለም አበበ የአፍሪካ ወንጌላውያን ተማሪዎች ኅብረትን እንዲመራ ኀላፊነት ተሰጠው

November 1, 2017
ዘላለም አበበ የአፍሪካ ወንጌላውያን ተማሪዎች ኅብረትን እንዲመራ ኀላፊነት ተሰጠው

የቀድሞ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ተማሪዎችና ምሩቃን ማኅበር (ኢቫሱ) ዋና ጸሐፊ የነበረው አቶ ዘላለም አበበ፣ ለዓለም አቀፉ የወንጌላውያን ተማሪዎች ኅብረት (IFES-EPSA) የአፍሪካ ዋና ጸሐፊ ሆኖ ተሰየመ፡፡ ሹመቱን ተከትሎም የተቋሙ ጽሕፈት ቤት ከናይጄሪያ ወደ አዲስ አበባ እንደሚዘዋወር ለማወቅ ተችሏል፡፡

ኀላፊነቱን ከዛሬ ኖቬምበር 1 ቀን፣ 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ሙሉ በሙሉ የሚጀምረው አቶ ዘላለም፣ ከትላንት በስቲያ በታንዛኒያ ዳሬ ሰላም የርክክብ ሥነ ሥርዐት ፈጽሟል፡፡ ዘላለም ለዚህ ኀላፊነት ከመብቃቱ ቀደም ብሎ የተቋሙ ተባባሪ ጸሐፊ በመሆን የሚሲዮን እና ደቀ መዝሙር ሥራ ክፍልን ለጥቂት ጊዜ ያህል በማስተባበር ላይ ሲሠራ እንደ ቆየ በሹመት ደብዳቤው ላይ ተጠቅሷል፡፡

አቶ ዘላለም አበበ በተማሪዎች አገልግሎት ውስጥ ከዐሥራ ስድስት ዓመታት በላይ ሲሳተፍ ከመቆየቱም በላይ፣ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ተማሪዎችና ምሩቃን ማኅበር (ኢቫሱ) ዋና ጸሐፊ በመሆን ለዘጠኝ ዓመታት አገልግሏል፡፡

ዓለም አቀፍ የወንጌላውያን ተማሪዎች ኅብረት (IFES)፣ እ.አ.አ. በ1947 ዓ.ም. የተቋቋመ ነው። ተቋሙ በመቶ ስድሳ አገራት ላይ የሚገኙና ቊጥራቸው ስድስት መቶ ሺህ የሚደርሱ የወንጌላውያን ክርስትና አማኝ የሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎችን በማስተባበር ላይ ሲሆን፣ ተማሪዎችን በወንጌል በመድረስ በጎ ተጽእኖ እንዲያመጡ የሚል ራእይ ሰንቆ የሚሠራ ዓለም አቀፍ አገልግሎት ነው፡፡ መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ የሚደርሱትን ተማሪዎች የሚያስተባብረው አሁን ዘላለም እንዲመራ ኀላፊነት የተሰጠው የአፍሪካው ቢሮ (EPSA) ነው፡፡

Add comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Latest News

ስለ ቤተ መጻሕፍት አደረጃጀት ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ሥልጠና ተሰጠ

“የቤተ መጻሕፍት አደረጃጀት” የተሰኘ የግማሽ ቀን ሥልጠና ለተለያዩ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ተወካዮች ተሰጠ። በሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ አዘጋጅነት የተዘጋጀው ሥልጠና፣ ቅዳሜ ሚያዚያ 14 ቀን፥ 2015 ዓ.ም. በላቭ ኤንድ ኬር ማዕከል የተካሄደ ነበር። 

Read More »
SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.