[the_ad_group id=”107″]

“ሺፈራው በፊደላት ሥዕል” በሚል ርእስ ለንባብ በቀረበው መጽሐፍ ላይ የተደረገው ግምገማ ሁለተኛው ክፍል እንደሚከተለው ቀርቧል።

2 comments

Your email address will not be published. Required fields are marked *

  • በአገራችን ግለ ታሪክ መፃፍ የተስፋፋው ትህነግ ሥልጣን ከያዘ እና የጎሣ ፌዴራሊዝምን ካቋቋመ ወዲህ ነው። ከጠባብ ብሔረተኛ አመለካከት እና ከግል መንፈሳዊ ልምምድ አስተምህሮ መራባት ጋር ይያያዛል። ዛሬ ቴክኖሎጂ ግለኛነትን፣ ልኩን ባለመነጋገር፣ ላለማስቀየም መወዳደስን መደበኛ አድርጎታል። ቶክ ሾው፣ አይዶል፣ “አድናቂህ/ሽ ነኝ” ባህል፣ ወዘተ። የአማንያኑ ቢበዛ እንጂ ከዓለማውያኑ አይተናነስም።

    አንዳንዴም፣ የተፈራ ታዛቢ መሞቱ ከተረጋገጠ በኋላ በተቀመሙ ትርክቶች ደርጅቶ የሚሸጥ ግለ ታሪክ አለ። በሌላ ጊዜ፣ ከተራው ዜጋ ራቅ ለማድረግ ሲባል በእንግሊዝኛ ታትሟል። ካስፈለገም፣ የማይቀመስ ዋጋ ጭኖ (ወዲያውም ትርፍ ፍለጋ) ብቅ ብሏል። የትምህርት ጥራት መውደቅ፣ ከቋንቋ ፖሊሲ ጋር ተመሣጥሮ፣ ረጅም ምንባብ ማንበብ ላልለመደ ትውልድ ማግለያ ተደርጓል።

    በቀድሞ ዘመን፣ ራስን ማተለቅ ስለሚመስል ግለ ታሪክ አይታሰብም፤ እንዲያውም ነውር ነው። ከዚህ የተነሳ ብዙ ሊዘገቡ የተገባቸው ገድሎች፣ ታሪኮች ለትውልድ ሳይተላለፉ ባክነዋል። በወንጌል አማኞች ዘንድ ይሁን በዓለማውያን፣ ግለ ታሪክ ውዳሴ እና አምልኮ መስሏል። ኢትዮጵያዊ አእምሮ ከአምልኮ ይፀዳል ማለት ኢትዮጵያዊነትን መካድ ነው! ጊዜ ካላችሁ፣ የየመፃሕፍቱን ርእስ ተመልከቱ።

    እስከ ዛሬ ካነበብዃቸው ግለ ታሪኮች መሓል በጥራት እና በይዘት ከፍተኛ ደረጃ የሰጠሁት፣ የፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላን “ከጉሬዛም ማርያም እስከ አዲስአበባ” መጽሐፍ ነው። ድግስ በሉት። ለምን? በአንድ ዋነኛ ምክንያት ብቻ፦ ደራሲው (ሽብሩ) እንደ አገር አስጎብኚ፣ አንባቢው እንደ አገር ጎብኚ መደረጋቸውና፣ ግለ ታሪክ በቀላል አማርኛ የዘመኑን አኳኋን ለማዋዣ መዋሉ ነው!

    አቶ ሽፈራው ወ/ሚካኤል ከአፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ እስከ አብዮታዊ ደርግ እስከ ዛሬ ዋነኛ አገራዊ (ቤተ ክርስቲያንን ጨምሮ) እና ዓለም አቀፋዊ ነውጦችና ለውጦችን ከፊት መቀመጫ ሆነው ሲመለከቱ የኖሩ ናቸው። “መንፈሳዊ” ለማድረግ በመሞከር ውስጥ ያ ሁሉ ታሪካዊ የእውቀት እና የልምድ ሃብት ባክኖ እንዳይሆን እሰጋለሁ።

    • ይቅርታ፣ መጨረሻው ላይ “ሲመለከቱ” ብሎ “ሲሳተፉና ሲቀርፁ” ይታከልበት።

SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.