[the_ad_group id=”107″]

ለማነጽ እንሠራለን!

ሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር፣ ወንጌላዊት የሆነችው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን፣ ክርስቶስን መስላ እንድታድግ በሚደረገው የማነጽ ሂደት ውስጥ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት በሚል በ2005 ዓ.ም. የተቋቋመ መንፈሳዊ ማኅበር ነው። “ሕንጸት” የግዕዝ ቃል ሲሆን፣ “ማነጽ” ወይም “መገንባት” የሚለውን ፍቺ ይይዛል።

ራእይ

የወንጌላውያን ክርስቲያን ማኅበረ ሰብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ በሆነ ክርስቲያናዊ አስተምህሮ እና ሥነ ምግባር ላይ ታንጾ የወንጌል ተልእኮውን ሲወጣ ማየት።

ተልእኮ

የኢትዮጵያ ወንጌላዊው የክርስቲያን ማኅበረ ሰብ ታላቁን ተልእኮ በሚፈጽምበት ሂደት ውስጥ፣ መልካም ዕድሎቹንም ሆኑ የሚጋፈጣቸውን ፈተናዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ በሆነ ክርስቲያናዊ አስተምህሮ ላይ በመመሥረትና ከዚሁ በሚመነጨው ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ላይ በመገንባት ምላሽ እየሰጠ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት ተጽእኖ በምድር ላይ እንዲንሠራፋ የበኩሉን ዕገዛ ማድረግ ነው።

ዝርዝር ዐላማዎቹም

 • ለመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣን የሚገዛ፣ የሕይወት መመሪያውንም የእግዚአብሔርን ቃል ያደረገ አማኝ ማኅበረ ሰብ እንዲኖር ተገቢውን ኀላፊነት መወጣት፤
 • በክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር የታነጸና ምሳሌ መሆን የሚችል አማኝ ማኅበረ ሰብ እንዲኖር ማገዝ፤
 • በኅብረተ ሰባዊ መስተጋብሩ ንቁና ክርስቲያናዊ ኀላፊነቱን ሊወጣ የሚችል አማኝ ማኅበረ ሰብ እንዲበራከት እገዛ ማድረግ፤
 • ለእግዚአብሔር ሉዐላዊነት ቅድሚያ በመስጠት አመክንዮአዊ አስተሳሰብን የሚያዳብር አማኝ ማኅበረ ሰብ እንዲጎለብት መጣር።

ዕሴቶቻችን

ክርስቶስን ማእከል ያደረገን፣ ለእግዚአብሔር ቃል ሥልጣን የምንገዛ፣ ለማገልገል የምንተጋ፣ በትብብር የምንሠራ፣ ለልዕቀት እና ለሐቀኝነት የቈምን ነን።

እነዚህን ዝርዝር ዐላማዎች ለመፈጸምና የሚፈለገውን ግብ ለመምታት፣ አማኝ ማኅበረ ሰቡን በሚመለከቱ ማናቸውም ጕዳዮች ላይ “ሐሳብ አፍላቂ/አመንጪ” (Christian Think-tank) የሆነ ተቋም መገንባትን ነው። ይህም ተቋም ተልእኮውን ለመፈጸም የሚከተሉትን ሦስት ዋና ዋና መንገዶችን ይጠቀማል፦

 • የብዙኃን መገናኛ (ኅትመት/ኤሌክትሮኒክ/ዲጂታል)
 • ምርምር፣ ሥልጠና እና ኅትመት
 • የውይይት መድረኮች

ለበለጠ መረጃ በሚከተሉት አድራሻዎች ይጠቀሙ፡-

ስልክ ቁጥር፡- +251-93-001-1441 
የፖስታ ሣጥን ቁጥር፡- 14049 አዲስ አበባ

ኢሜል፡- 
info@hintset.org
hintsetchristiansociety@gmail.com
hintsetbookclub@gmail.com

About Hintset

Hintset Christian Society is a faith-based society founded in June 7, 2013 by a group of Christians who are committed to the expansion and edification of the Evangelical Churches of Ethiopia. The Ge’ez word ‘Hintset’, which means ‘to edify’ or ‘to build’, is intended to describe this commitment.

Vision

Hintset Christian Society seeks to foster Biblical knowledge and Christian values to equip Ethiopian Evangelical Christians to fulfill the Gospel mandate.

Mission

Hintset Christian Society is there to fill the gaps that the Ethiopian Evangelical Community faces in its pursuit of fulfilling the Great Commission in Ethiopia and beyond, by contributing positively in seizing its opportunities and overcoming the challenges, in a way that is Biblical and reflective of Christian ethics.

Objectives

 • To foster submission to the authority of the Bible and acceptance of the word of God as a guide for life among evangelical believers
 •  To advance Christian values so as to develop an exemplary faith community
 • To encourage socially awareness and support responsible Christian values so as to develop an exemplary faith community and faith based social action
 • To strive to enhance critical reflection and theological thinking which promotes the Sovereignty of God.

Values

 • Christ-centered
 • Adhere to the authority of the Scripture
 • Dedicated to service
 • Seek to work in collaboration 
 • Strive to excellence 
 • Stands for integrity 

Hintset believes the best way to achieve its objectives is through developing a Christian Think-Tank geared to address any issues related to the Christian faith and the believing community. To fulfill its mandate the institution intends to utilize the following means:
 

 1. 1. Mass Media (Print/Electronic/Digital)
 2. 2. Research, Training, and Publication (RTP)
 3. 3. Forum/Events


How You Can Get Involved:

Hintset Christian Society cordially requests that individuals and organizations which share its vision to support its efforts.

If you have any questions about our ministry or want to find out how you can get involved, please contact us through any of the following:

Contact Person: 
Tel: +251-93-001-1441
P.o.Box: 14049 – Addis Ababa

Email:
info@hintset.org
hintsetchristiansociety@gmail.com
hintsetbookclub@gmail.com

ሕንጸት መጽሔት

ሕንጸት መጽሔት የሚኖረው ይዘት ከአሳታሚው እምነትና ፍልስፍና የሚመነጭ ነው፡፡ መጽሔቱ በወንጌል አማኝ ማኅበረ ሰቡ ዘንድ ትልቅ ተነባቢነትና ተኣማኒነት ያለው፣ አገልግሎቱም ዘመን ዘለቅ እንዲሆን ይጠበቃል፡፡ በመሆኑም፣ ተቀባይነትና ዘላቂ ዕድሜ ያለው አገልግሎት ለመስጠት በሥራ ልዕቀት የሚያምን፣ ከክርስትና እምነት ጋር የሚጣጣም የጋዜጠኝነት ተግባራትን የሚጠቀም፣ የአማኝ ማኅበረ ሰቡን ውስጣዊም ሆኑ ውጫዊ ተግዳሮቶች በድፍረትና በጥበብ የሚያነሣ፣ ለአመክንዮ ትልቅ ስፍራን የሚሰጥና አማኝ ማኅበረ ሰቡን በዚህ መንገድ ለመቅረጽ እንዲሁም የአማኝ ማኅበረ ሰቡ ድምፅ የመሆን ግብ ሰንቆ የሚዘጋጅ ነው፡፡

ጥናት እና ምርምር

ይህ የአገልግሎት ክፍል የሚተገብረው፣ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናትን በሚመለከቱ ማናቸውም ጉዳዮች ላይ የምርምርና የጥናት ሥራዎችን ማከናውን ነው። ማኅበሩ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ውስጥ የተሰማሩ ወገኖችን በማሳተፍ፣ በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ጥናቶችና ምርምሮች እንዲደረጉ ያመቻቻል፤ የተደረጉ ጥናቶችና ውጤቶቻቸውን ለሚመለከታቸው አካልት ያቀርባል፤ ያሳትማል።

ሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ

የሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ፣ በክርስቲያን ማኅበረ ሰቡ ዘንድ የንባብና የውይይት ባሕል እንዲዳበርና ብርቱ ጸሐፊያን እንዲጎለብቱ በሚል በወር አንድ ጊዜ የሚደረግ የመጽሐፍ ግምገማ/ውይይት ያካሄዳል፡፡

የእምነት መግለጫ

ሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር ከዚህ በታች በተጠቀሱ የክርስትና አእማድ የእምነት አቋሞች ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ አገልግሎቱም በእነዚህ መሠረታውያን የእምነት አናቅጽ ውስጥ በተካተቱ አስተምህሮዎች የተገራ ነው፡፡

SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.