[the_ad_group id=”107″]
ማቴቴስ ትሰኝ የነበረችውን መጽሔትና መላውን ብርዕ ጨባጮቿን ጥረት እያሰላሰልሁ፣ ደግሞም ሕንጸት ይሏትን ዐዲስ መጽሔት መከሠት እያሰብሁ በነበረበት አንዲት ምሽት እንዲህ፣ እንዲህ ሲሰማኝና እንዲህ፣ እንዲህ በሐሳብ ስዛቍን (ስለፋ) አመሸሁ። መጽሔቶቹም የሕይወትን ትዝታና ተስፋ በግርድፉ የማነጽርባቸው ጊዜያዊ ትእምርቶች መስለው ታዩኝ። ሐሳቤ ታዲያ ወደ ኋላና ወደ ፊት መንጠሩ አልቀረም፤ ማቴቴስ ከኋላ ሕንጸት ከፊት ለፊት። ማቴቴስ አሁን በኅትመት ላይ አይደለችምና “የት ገባች” የማለትን ነገር ብትጠይቁኝ፣ መልሱን በይፋ ለመስጠት ዕውቀቱም ሥልጣኑም የለኝም። በመገኘቷ ዘመን ልሳኗን ይዋስ እንደ ነበረ ጸሐፊ ብቻ፣ ባለመገኘቷ የሚሰማኝን አንዳች ግላዊ ስሜትና ተዛምዶኣዊ ትምህርት (lesson) መተንፈሴ አይቀሬ ኾኖብኝ ነው። ስለ ሕንጸት ደግሞ በተስፋ ደስ ቢለኝ የሞነጨርኩት ታክሎበት የቀረበ ነው። እነሆ በረከት…
ሕንጸት ከልደት (ገና) በዓል በፊት ቀጣዩ ቅጿ እንደማይደርስ በማሰብ ዛሬውኑ “እንኳን አደረሳችሁ” ማለቴ የወግ ነው። ከመልካም ምኞት መግለጫዬ በላይ ግን የክብረ በዓሉን ምክንያት በዚህ መልኩ ብናየው በማለት ይህችን ከትቤአለሁ። ጥያቄና መልስ።
የምወድህ (የጽሑፍ ልማድ ኾኖ እንጂ አንቺም አለሽበት) አንባቢዬ ሆይ፣ “ምን ላንብብ? ለማንስ ላስተላልፋት?” እንደምትለኝ እገምታለሁ። ይህችን መጣጥፍ ለመጫር ምክንያት የኾነኝን ነገር መጨረሻ ላይ ነው የምነግርህ። በቅድሚያ ስለ ንባብ/ ማንበብ ጥቂት እንድጫጭር እያነበብህ ፍቀድልኝ።
ልጆች ሳለን በሚነገሩን ጣፋጭ ተረቶች በኩል አጮልቀን የምናያቸው የሕልም ዓለማት ነበሩን። (ርግጥ፣ በነ “አያ ጅቦ” ታሪክ ብቻ ላደገ ልጅ ይህ አባባል አይሠራም።)
Hintset Christian Society is a faith-based society founded in June 7, 2013 by a group of Christians who are committed to the expansion and edification of the Evangelical Churches of Ethiopia. The Ge’ez word ‘Hintset’, which means ‘to edify’ or ‘to build’, is intended to describe this commitment.
“ከመልእክተ ሕንጸት” በስተቀር፣ በድረ ገጹ ላይ የሚቀርቡ ማናቸውም ዝግጅቶች የሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር አቋምን ላይወክሉ ይችላሉ።
With the exception of “Hintset’s Editorial”, any pubication presented on the Website may not necessarily represent the position of Hintset Christian Society.

Hintset Christian Society
Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.