[the_ad_group id=”107″]

ሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ

የሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ፣ በክርስቲያን ማኅበረ ሰቡ ዘንድ የንባብና የውይይት ባሕል እንዲዳበርና ብርቱ ጸሐፊያን እንዲጎለብቱ በሚል በወር አንድ ጊዜ የሚደረግ የመጽሐፍ ግምገማ/ውይይት ያካሄዳል፡፡

በዚህም የሚከተሉትን ዝርዝር ዓላማዎችን ለማሳካት ይሠራል፡-

  • የንባብ ባሕል እንዲዳብር የበኩሉን ድርሻ መወጣት፤
  • ክርስቲያን ጸሐፊያን እንዲበራከቱ ማበረታታት፤
  • የሚታተሙ መጻሕፍት ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ሒሳዊ ምልከታዎችን በማቅረብ ማገዝ፤
  • በክርስቲያን ማኅበረ ሰቡ መካከል የውይይት ባሕልን ማዳበር፤

 

ለግምገማ የሚቀርቡ መጻሕፍ ከሞላ ጎደል የሚከተሉት ይሆናሉ፡-

  • በዋናነት የወንጌል አማኝ ማኅበረ ሰቡን የሚመለከቱ ሆነው ሲገኙ፤
  • የመጻሕፍቱ ፋይዳ ጉልሕ ሆኖ ሲገኝና ይህም አሳማኝ በሆነ መልኩ መብራራት ሲችል፤
  • በተቻለ መጠን ደረጃቸውን የጠበቁና ʻሊነበቡ ይገባቸዋልʼ ተብለው የሚታመነባቸው ሥራዎች ሊሆኑ ይገባል፤
  • ጻሓፍቱ በአማኝ ማኅበረ ሰቡ ውስጥ ያላቸው ተደማጭነት ጉልሕ ሆኖ ሲገኝ ዕድል ሊሰጠው ይችላል፤
  • የወንጌል አማኝ ማኅበረ ሰቡን በክፉም ሆነ በደግ የሚመለከቱና በማናቸውም አካላት የተጻፉ ሥራዎች ሲገኙ፤
  • ወቅታዊና አንገብጋቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የተጻፉ መጻሕፍት ሲኖሩ፤

ከላይ የተዘረዘሩት መሥፈርቶች በየትኛውም የሥነ ጽሑፍ ዘውግ ውስጥ ያሉትን መጻሕፍት ይመለከታል፡፡

የሕንጸት መጽሐፍ ክበብ አባል ይሁኑ

ከዚህ በፊት የነበሩ የመፅሐፍ ቅኝቶች

“ሐዋሪያነትና ነብይነት”፦ የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ቲዮሎጂካል ኮሚሽን | ለውይይት ጽሑፍ አቅራቢ – ሶፋኒት አበበ (ዶ/ር)

በሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ፣ በሚያዚያ ወር ለውይይት ቀርቦ የነበረው፣ “ሐዋሪያነትና ነብይነት” የተሰኘው መጽሐፍ ግምገማ የመጀመሪያው ክፍል እንደሚከተለው ቀርቧል።

Read More »

“ጴንጤቆስጤአዊነት ወይስ የብልጽግና ወንጌል?” ፦ ዕሸቱ አበበ (መጋቢ) | የታዳምያን ውይይት

በሐምሌ ወር የመጽሐፍ ግምገማ መርሐ ግብር፣ “ጴንጤቆስጤአዊነት ወይስ የብልጽግና ወንጌል?” በሚል ርእስ በመጋቢ ዕሸቱ አበበ ተጽፎ፣ በዳዊት ሙራ ኂስ የተሰጠበትን መጽሐፍ የውይይት ክፍል ይመልከቱ።

Read More »

“ጴንጤቆስጤአዊነት ወይስ የብልጽግና ወንጌል?”፦ ዕሸቱ አበበ (መጋቢ) | ለውይይት መነሻ ጽሑፍ አቅራቢ – ዳዊት ሙራ

“ጴንጤቆስጤአዊነት ወይስ የብልጽግና ወንጌል?” በሚል ርእስ በመጋቢ ዕሸቱ አበበ የተጻፈውንና በዳዊት ሙሩ ኂስ የተሰጠበትን የሐምሌ ወር የመጽሐፍ ግምገማ መርሓ ግብር የመጀመሪያ ክፍል ይመልከቱ።

Read More »

“ሐተታ ዘዘርአ ያዕቆብ በሚባል ስም የሚታወቀው የወርቄ የሕይወት ታሪክ”፦ ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ | የታዳምያን ውይይት

ሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ በወርኀዊ መርሐ ግብሩ፣ “ሐተታ ዘዘርአ ያዕቆብ በሚባል ስም የሚታወቀው የወርቄ የሕይወት ታሪክ” በሚል ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ከግእዝ ወደ አማርኛ በተረጐሙት ሥራ ላይ

Read More »

“ሐተታ ዘዘርአ ያዕቆብ በሚባል ስም የሚታወቀው የወርቄ የሕይወት ታሪክ”፦ ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ | ለውይይት መነሻ ጽሑፍ አቅራቢ – አባ ዳዊት ወርቁ (ዶ/ር)

ሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ በወርኀዊ መርሐ ግብሩ፣ “ሐተታ ዘዘርአ ያዕቆብ በሚባል ስም የሚታወቀው የወርቄ የሕይወት ታሪክ” በሚል ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ከግእዝ ወደ አማርኛ በተረጐሙት ሥራ ላይ

Read More »

“ዕቅበተ እምነት በኢትዮጵያ ዐውድ”፦ ዳንኤል ይልማ | የታዳምያን ውይይት

ሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ በግንቦት ወር ለውይይት አቅርቦት የነበረውና “ዕቅበተ እምነት በኢትዮጵያ ዐውድ” የተሰኘው መጽሐፍ ሦስተኛው ክፍል፣ ከታዳምያን ለተነሡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተሰጡ ምላሾች እንደሚከተለው ቀርበዋል።

Read More »

“ዕቅበተ እምነት በኢትዮጵያ ዐውድ”፦ ዳንኤል ይልማ | ለውይይት መነሻ ጽሑፍ አቅራቢ – ሩሃማ ገዛኸኝ

ሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ በግንቦት ወር ለውይይት አቅርቦት የነበረውና “ዕቅበተ እምነት በኢትዮጵያ ዐውድ” የተሰኘው መጽሐፍ ሁለተኛው ክፍል፣ ሩሃማ ገዛኸኝ ያቀረበችውን ግምገማ ይዞ እንደሚከተለው ለዕይታ ቀርቧል።

Read More »

“ዕቅበተ እምነት በኢትዮጵያ ዐውድ”፦ ዳንኤል ይልማ | ለውይይት መነሻ ጽሑፍ አቅራቢ – ተካልኝ ዱጉማ (ዶ/ር)

ሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ በግንቦት ወር መርሓ ግብሩ ለውይይት አቅርቦት የነበረውና፣ “ዕቅበተ እምነት በኢትዮጵያ ዐውድ” የተሰኘው መጽሐፍ ግምገማ የመጀመሪያ ክፍል ዶ/ር ተካልኝ ዱጉማ ያቀረቡትን ኂስ ይዟል፤

Read More »

“ዐብረን ሰው እንሁን፦ የግጭት ልውጠት መሠረታውያን”፦ ሰሎሞን ጥላሁን | የታዳሚያን ውይይት

ሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ፣ በሚያዚያ ወር መርሓ ግብሩ ለውይይት አቅርቦት የነበረውና፣ “ዐብረን ሰው እንሁን” የተሰኘው የሰሎሞን ጥላሁን መጽሐፍ ግምገማ፣ ሁለተኛው የውይይት ክፍል እንደሚከተለው ቀርቧል።

Read More »

ስለ ቤተ መጻሕፍት አደረጃጀት ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ሥልጠና ተሰጠ

“የቤተ መጻሕፍት አደረጃጀት” የተሰኘ የግማሽ ቀን ሥልጠና ለተለያዩ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ተወካዮች ተሰጠ። በሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ አዘጋጅነት የተዘጋጀው ሥልጠና፣ ቅዳሜ ሚያዚያ 14 ቀን፥ 2015 ዓ.ም. በላቭ ኤንድ ኬር ማዕከል የተካሄደ ነበር። 

Read More »

የመምህር ጽጌ “ይነጋል” ውይይት ተካሄደበት

በሕንጸት ክርስቲያናዊ ማኅበር አዘጋጅነት በየወሩ የሚካሄደው ሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ እሑድ መስከረም 8 ቀን፣ 2009 ዓ.ም. ተካሄደ፡፡ በኢትዮጵያ ሥነ መለኮት ድኅረ ምረቃ ት/ቤት አዳራሽ በተከናወነው መርኀ ግብር፣ ለውይይት የቀረበው መጽሐፍ “ይነጋል” የተሰኘውና በዲያቆን ጽጌ ሥጦታው የተጻፈው መጽሐፍ ሲሆን፣ የውይይት መነሻ ሐሳብ ያቀረቡት ቀሲስ ሰሎሞን ደረጀ ናቸው፡፡

Read More »

“ሌላ ሰው” ለውይይት ቀረበ

ወርኀዊው የሕንጸት መጽሐፍ ክበብ የግምገማ መርሓ ግብር እሑድ ሐምሌ 3 ቀን፣ 2008 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሥነ መለኮት ድኅረ ምረቃ ት/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሄደ፡፡ በዕለቱ ለውይይት የቀረበው መጽሐፍ “ሌላ ሰው” የተሰኘው የዶ/ር ምሕረት ደበበ የልብ ወለድ ሥራ ነው፡፡

Read More »

“ቱንቢ” የተሰኘው መጽሐፍ ለውይይት ቀረበ

በሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ አዘጋጅነት በየወሩ የሚካሄደው የመጽሐፍ ግምገማ መርሓ ግብር ባለፈው እሑድ ሰኔ፣ 5 ቀን 2008. ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሥነ መለኮት ድኅረ ምረቃ ት/ቤት አዳራሽ ተከናወነ፡፡ የወሩ ተረኛ መጽሐፍ የነበረው በመርዓዊ ንጉሤ የተጻፈውና “ቱንቢ፡- መለኪያውን የማያውቅ ልኩን አያውቅም” የተሰኘው መጽሐፍ ነበር፡፡

Read More »

የመጋቢ ስሜ ታደሰ መጽሐፍ ውይይት ተካሄደበት

ሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ የወርኀ ጥር የመጽሐፍ ግምገማ መርሓ ግብሩን አካሄደ፡፡ እሑድ ግንቦት 7 ቀን፣ 2008 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ድኅረ ምረቃ ት/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው ግምገማ ላይ ለውይይት የቀረበው መጽሐፍ “ምን ሠርተን እንለፍ?” የተሰኘውና በመጋቢ ስሜ ታደሰ የተዘጋጀው ነው፡፡

Read More »

“የአመራር ጥበብ” መጽሐፍ ለውይይት ቀረበ

“የአመራር ጥበብ” የተሰኘውና በአቶ ጌታቸው በለጠ የተጻፈው መጽሐፍ በሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ ውይይት ተደረገበት፡፡ ውይይቱ ባለፈው እሑድ፣ የካቲት 6 ቀን፣ 2008 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሥነ መለኮት ድኅረ ምረቃ ት/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ነበር የተካሄደው፡፡

Read More »

“ክርስትና ለጠያቂ አእምሮ” የተሰኘው መጽሐፍ ውይይት ተካሄደበት

ወርኀዊው የሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ መርሓ ግብር፣ ባለፈው እሑድ ጥር 1 ቀን፣ 2008 ዓ.ም. በኢትዮጵያ የሥነ መለኮት ድኅረ ምረቃ ት/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሄደ፡፡ ለውይይት ቀርቦ የነበረው መጽሐፍ በእንግሊዛዊው ጸሐፊ ሲ.ኤስ. ሊዊስ “Mere Chrsitianity” ተብሎ የተጻፈውና በአዲስ አሰፋ “ክርስትና ለጠያቂው አእምሮ” በሚል ወደ አማርኛ የተመለሰው መጽሐፍ ነው፡፡

Read More »

“ጉርሻ እና ፌሽታ” የተሰኘው የኃይል ከበደ መጽሐፍ ለውይይት ቀረበ

በሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ አዘጋጅነት በየወሩ የሚካሄደው የመጽሐፍ ውይይት ባለፈው እሑድ ታኅሣሥ 3 ቀን፣ 2008 ዓ.ም. ተካሄደ፡፡ ለውይይት የቀረበው መጽሐፍ በኃይል ከበደ የተጻፈው “ጉርሻ እና ፌሽታ” የተሰኘው መጽሐፍ ሲሆን፣ የውይይት ሐሳብ አቅራቢው ደግሞ አቶ አስናቀ እንድሪያስ ነው፡፡

Read More »

“ፈለገ ብርሃኑ” የተሰኘው መጽሐፍ በሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ ውይይት ተደረገበት

“ፈለገ ብርሃኑ” የተሰኘው መጽሐፍ በሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ አዘጋጅነት በሚካሄደው ወርኀዊ የመጽሐፍ ግምገማ መርኀ ግብር ላይ ቀርቦ ውይይት ተደረገበት፡፡ እሑድ ኅዳር 5 ቀን፣ 2008 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሥነ መለኮት ድኀረ ምረቃ ት/ቤት መሰብሰቢያ አደራሽ በተደረገው በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የመጽሐፉ ጸሐፊ ተገግኝቶ ለቀረቡለት ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥቷል፡፡

Read More »

ሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ “ወፍ ማስፈራሪያ እና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች” የተሰኘውን መጽሐፍ ለውይይት አቀረበ

ሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ በመስከረም 2008 ዓ.ም. ወርኀዊ መርሓ ግብሩ የሚካኤል ሽፈራውን “ወፍ ማስፈራሪያ እና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች” የተሰኘውን መጽሐፍ በኢትዮጵያ ሥነ መለኮት ድኅረ ምረቃ ት/ቤት መሰብሰቢያ አደራሽ ለውይይት አቀረበ፡፡

Read More »

ሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ የወርኀ ጥር የመጽሐፍ ግምገማ መርሓ ግብሩን አካሄደ፡፡

ሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ የወርኀ ጥር የመጽሐፍ ግምገማ መርሓ ግብሩን አካሄደ፡ እሑድ ጥር 3 ቀን፣ 2007 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ድኅረ ምረቃ ት/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው ግምገማ ላይ ለውይይት የቀረበው መጽሐፍ “እኔን ማን ትሉኛላችሁ?፡- ክርስቶስ እና የማዳን ሥራው” የተሰኘውና በበልሁ ደለለኝ የተዘጋጀው መጽሐፍ ነው፡፡

Read More »
SIGN UP FOR OUR NEWSLETTER.

Hintset’s latest news and articles of the week to encourage, challenge, and inform you.